YoVDO

ኮቪድ-19ን ጨምሮ አዳዲስ የመተንፈሻ አካላት ቫይረሶችን የመለየት፣ የመከላከል፣ ምላሽ የመስጠትና እና መቆጣጠርያ ዘዴዎች

Offered By: OpenWHO

Tags

COVID-19 Courses Public Health Courses Infection Prevention Courses Emergency Response Courses

Course Description

Overview

አጠቃልሎ፥ ኮሮና ቫይረሶች ከተለመደው ጉንፋን ጀምሮ ይበልጥ ከባድ እስከሆኑት እንደመካከለኛው ምስራቅ የመተንፈሻ አካላት ሲንድሮም (ሜርስ) እና ከባድ አጣዳፊ የመተንፈሻ አካላት ሲንድሮም (ሳርስ) ያሉ በሽታዎችን እንደሚያመጡ የሚታወቁ ሰፊ የቫይረሶች ቤተሰብ ናቸው።

ኖቭል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተገኘው በ2019 በውሃን፣ ቻይና ውስጥ ነበር። ይህ ከዚህ በፊት በሰዎች ውስጥ ያልተገኘ አዲስ ኮሮና ቫይረስ ነው።

ይህ ትምህርት ስለኮቪድ-19 እና አዳዲስ የመተንፈሻ አካላት ቫይረሶች አጠቃላይ መግቢያ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ለህብረተሰብ ጤና ባለሙያዎች፣ ለድንገተኛ ክስተት አስተዳደሮች እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በአለም አቀፍ ድርጅቶች እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች ታሰቦ የተዘጋጀ ነው።

ኦፊሴላዊው የበሽታው መጠሪያ ከቁሳቁስ ዝግጅት በኋላ የተሰጠ በመሆኑ፣ ‹ኤንኮቭ› ተብሎ የተጠቀሰ ማንኛውም ነገር በቅርብ ጊዜ በተገኘው ኮሮና ቫይረስ የተከሰተውን ተላላፊ በሽታ ኮቪድ-19 ያመለክታል

እባክዎን የዚህ ኮርስ ይዘት በጣም የቅርብ ጊዜ መመሪያን ለማንፀባረቅ እየተከለሰ ነው። በሚከተሉት ኮርሶች ውስጥ በተወሰኑ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተዘመነ መረጃ ማግኘት ትችላለህ፡

ክትባት፡ የኮቪድ-19 ክትባቶች ቻናል

የአይፒሲ እርምጃዎች፡ አይፒሲ ለኮቪድ-19

አንቲጅን ፈጣን የምርመራ ምርመራ፡ 1) SARS-CoV-2 አንቲጅን ፈጣን የምርመራ ምርመራ; 2) ለ SARS-CoV-2 አንቲጅን RDT ትግበራ ቁልፍ ጉዳዮች


Syllabus

Course information

ይህ ኮርስ በሚቀጥሉት ቋንቋዎችም ይገኛል: -

English - français - Español - 中文 - Português - العربية - русский - Türkçe - српски језик - فارسی - हिन्दी, हिंदी - македонски јазик - Tiếng Việt - Indian sign language - magyar - Bahasa Indonesia - বাংলা - اردو - Kiswahili - ଓଡିଆ - Hausa - Tetun - Deutsch - Èdè Yorùbá - Asụsụ Igbo - ਪੰਜਾਬੀ - isiZulu - Soomaaliga - Afaan Oromoo - دری - Kurdî - پښتو - मराठी - Fulfulde- සිංහල - Latviešu valoda - తెలుగు - Esperanto - ภาษาไทย - chiShona - Kreyòl ayisyen - Казақ тілі - தமிழ் - Ελληνικά

አጠቃላይ እይታ፥ ይህ ትምህርት ኖቭል ኮሮና ቫይረሶችን ጨምሮ ስለአዳዲስ የመተንፈሻ አካላት ቫይረሶች አጠቃላይ መግቢያ ይሰጣል። በዚህ ትምህርት ማጠናቀቂያ የሚከተሉትን ነጥቦች መግለፅ መቻል ይኖርበዎታል፦

  • የአዳዲስ የመተንፈሻ አካላት ቫይረሶችን ተፈጥሮ፣ እንዴት ወረርሽኝን መመርመር እና መገምገም እንደሚቻል፣ በኖቭል የመተንፈሻ አካላት ቫይረሶች ምክንያት የሚከሰቱ ወረርሽኞችን መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ስትራቴጂዎች፤
  • አዲስ የመተንፈሻ አካላት ቫይረስ በተከሰተ ጊዜ የተጋላጭነት መረጃን ለመለዋወጥ እና በሽታውን በመለየት፣ በመከላከል እና ምላሽ በመስጠት ተግባር ላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለማሳተፍ ምን አይነት ስትራቴጂዎችን መጠቀም እንደሚገባ

በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ይበልጥ ጠለቅ ብሎ ለመግባት እንዲያግዙዎ ከእያንዳንዱ ሞጁል ጋር ተያይዘው የቀረቡ ግብዓቶች አሉ።

የትምህርቱ አላማ፡ የአዳዲስ የመተንፈሻ አካላት ቫይረሶች መሰረታዊ መርሆዎችን እና ለወረርሽኝ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ ይግለፁ።

የትምህርቱ የጊዜ ፍጆታ፥ በግምት ወደ 3 ሰዓታት።

የምስክር ወረቀት፥ በዚህ ጊዜ የሚሰጥ ምንም የምስክር ወረቀት አይኖርም።

የተተረጎመዉ ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ቋንቋ Emerging respiratory viruses, including COVID-19: methods for detection, prevention, response and control, 2020 የአለም የጤና ደርጅት ለዚህ የትርጉም ስራ ይዘት ወይም ትክክለኛነት ኃላፊነት አይወስድም። በእንግሊዝኛዉ እና በአማረኛዉ ትርጉም መካከል ልዩነት ከተፈጠረ የመጀመሪያው የእንግሊዝኛ ስሪት አስገዳጅ እና ትክክለኛ ስሪት ይሆናል።

ይህ የትርጉም ስራ በአለም የጤና ደርጅት አልተረጋገጠም። ይህ ግባዓት ለትምህርት ድጋፍ ዓላማዎች ብቻ የታሰበ ነው።

Course contents

  • ሞጁል ሀ፥ ኮቪድ-19ን ጨምሮ የአዳዲስ የመተንፈሻ አካላት ቫይረሶች መግቢያ:

    አጠቃላይ የትምህርቱ ዓላማ፥ ኮቪድ-19ን ጨምሮ አዳዲስ የመተንፈሻ አካላት ቫይረሶች ለምን ለሰው ልጅ ጤንነት ሉላዊ ስጋት እንደሆኑ ማስረዳት መቻል
  • ሞጁል ለ፥ ኮቪድ-19ን ጨምሮ የአዳዲስ የመተንፈሻ አካላት ቫይረሶችን መለየት፥ ቁጥጥር እና የላቦራቶሪ ምርመራ:

    አጠቃላይ የትምህርቱ ዓላማ፥ አዲስ የመተንፈሻ አካላት ቫይረስ ወረርሽኝን እንዴት መለየት እና መገምገም እንደሚቻል መግለጽ
  • ሞጁል ሐ፥ የአደጋ ተጋላጭነት ተግባቦት እና የማህበረሰብ ተሳትፎ:

    አጠቃላይ የትምህርቱ ዓላማ፥ ስለአደጋ ተጋላጭነት መረጃ ለማስተላለፍ እና ኮቪድ-19 ለይቶ በማወቅ፣ በመከላከል እና ምላሽ በመስጠት ተግባር ላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለማሳተፍ ምን አይነት ስትራቴጂዎችን መጠቀም እንዲሚገባ መግለጽ
  • ሞጁል መ፥ ኮቪድ-19ን ጨምሮ አዲስ የመተንፈሻ አካላት ቫይረስን መከላከል እና ምላሽ መስጠት:

    አጠቃላይ የትምህርቱ ዓላማ፥ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኞችን ጨምሮ አዳዲስ የመተንፈሻ አካላት በሽታ አምጪ ተዋህሲያንን የመከላከል እና መቆጣጠር ስትራቴጂዎችን መግለጽ።

Related Courses

Poisonings in the Home and Community: Assessment and Emergency Response
University of California, San Francisco via Coursera
生命安全与救援Life Safety and Rescue
Shanghai Jiao Tong University via Coursera
How to Save a Life: Pediatric Advanced Life Support
The Disque Foundation via edX
First Aid for Babies and Children
FutureLearn
Biosecurity and Bioterrorism: Public Health Dimensions
University of New South Wales via FutureLearn